Agape GLC is the official name of Glorious Life Church Teachings and Book ministry.

Vision

To spread teachings of the Bible and books written by Reverend Tezera Yared in order to deliver the world's nations from spiritual failure and guide them toward a life of excellence and glory.

Mission

Through the employment of variety of technologies and marketing techniques, spreading books, spiritual materials and messages prepared by Reverend Tezera Yared in the Glorious Life Church, first for the congregation there, then for the churches in Addis Ababa and other regional areas, and even around the world, highlighting their demand and transforming the lives of many through the messages

Purpose

To spread Reverend Tezera Yared's message to as many people as possible, making them partakers of his vision and grace while also creating a generation that fully embodies Christ, preaches the great good news for everyone, frees everyone from all forms of oppression, and creates a generation that will be influential in all spheres

Our Values

  • The provision of excellent service
  • Helpfulness and kindness
  • Delivery of effective and efficient service with hospitality
  • አጋፔ ጂ.ኤል.ሲ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን የትምህርቶች እና የመጽሐፍ አገልግሎት ኦፊሴላዊ ስም ነው ፡፡

    ራዕያችን

    በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ ተዘጋጅተው የሚቀርቡትን የእግዚአብሔር ቃል ትምህርቶች እና መጽሐፍቶች ወደ አለም ሁሉ ተደራሽ በማድረግ ሰዎችን ሁሉ ከመንፈሳዊ ውድቀት በማንሳት ወደ ከበረ እና ወደ ላቀ ሕይወት ማስገባት ።

    ተልዕኳችን

    የተለያዩ የቴክኖሎጂ እና የአሻሻጥ ጥበብን በመጠቀም የሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ ትምህርቶች፣ መጽሐፍትና የክብር ሕይወት ቤተክርስትያን የምታዘጋጃቸውን መንፈሣዊ ቁሶች፣ በቅድሚያ ለክብር ሕይወት ቤተክርስትያን አባላት ፣ በመቀጠል ለአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ላሉ ቤተክርስትያናት አልፎም በአለም ዙርያ ፣ ተፈላጊነታቸውን ማጉላት እንዲሁም በመልክቶቹ የብዙዎችን ሕይወት መቀየር ።

    ዓላማችን

    በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ ትምህርቶች እና መጽሐፍቶች ብዙዎችን በመድረስ የራእዩና የጸጋው ተካፋይ እንዲሆኑ በማድረግ ክርስቶስን በሙላት የሚወክል ትውልድ በማስነሣት ለሕዝብ ሁሉ የሚሆነውን ታላቁን የምስራች ወንጌል መስበክ ፣ ሰዎችን ሁሉ ከየትኛውም ዓይነት እስራት ነፃ ማውጣት ፣ በሁሉም አቅጣጫ ተጽዕኖ የሚፈጥር ትውልድ ማስነሣት ።

    እሴቶቻችን

  • የማይረሳ እና በሰዎች ልብ ውስጥ የሚቀር የላቀ አገልግሎት መስጠት
  • ትህትና ፣ ፈገግታ እና ቅልጥፍና የተሞላበት አገልግሎት መስጠት
  • ጊዜው ያመጣቸውን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የተለያዩ የሽያጭ ዘይቤዎችን መጠቀም