መስፋፋት | ENLARGEMENT

Br50.00

“እግዚአብሔርም ያፌትን ያስፋ፥ በሴምም ድንኳን ይደር፤ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።”
— ዘፍጥረት 9፥27

እግዚአብሔር በእኛ ሕይወት ለባለፈው እና ላለፉት አመታት ስላደረገልን መልካም ነገር ስናመሰግን ከፊታችን ባለው አመት መስፋፋት ያደርግልናል። መስፋፋት ማለት መስፋት፣ በመጠን መብለጥ፣ ገደቦችን አልፎ መሄድ፣ በወርድ ወይንም በጎን መርዘም እና በጅምላ መስፋፋት ነው።

To make greater in quality or dimension!

እግዚአብሔር አንዱ ያፌትን የባረከበት በረከት በመስፋፋት ነው። እግዚአብሔር ያፌትን ያስፋ ማለት ማስፋፋት (to dilate)፣ መጨመር (to increase) ማለትም በትልቁ ማደግ፣ አትክልት እንደሚያብበው ማበብ እና አንድ ፊኛ እስከ መጨረሻው እንደሚወጠረው መስፋት ማለት ነው።

እግዚአብሔር ሰዎችን በሁሉም አቅጣጫ ሁልጊዜ ማስፋት ይፈልጋል። እግዚአብሔር እኛን በማስፋት የበለጠ ሕይወታችንን ወይም አገልግሎታችንን ማሳደግ ይፈልጋል።
“እግዚአብሔር ያፌትን ያስፋ” ማለት ታላቅ ሕዝብ ያደርገዋል ማለት ነው። እንዲሁም መስፋፋት ማለት በ2ሳሙ 22፥37 ብዙ ድል እና ስኬት ማግኘት እንዲሁም የማያቋርጥና የማይፈርስ ስኬትን ማግኘት፣ በኢሳ 54፥1-3 ደግሞ ትልቅ ማድረግ ማስፋት ማራዘም ማደግ መጨመር፣ በመዝ 119፥32 በውስጥ ወይንም በልባችን የሆነ መስፋት ነው፣ 1ዜና 4፥10 የእኔን ግዛት ወይም መንቀሳቀሻ አስፋው ማለት ነው።

መስፋፋት በመንፈስ፣ በነፍስ እና በስጋ መስፋፋት ሲሆን የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳወጀልን ይህ 2017 ዓ.ም. የመስፋፋት አመታችን ነው።
የመስፋፋት አመት ማለት የማደግ፣ የመጨመር፣ የመጉላት፣ የጥልቀት፣ የመገንባት፣ ከገደብ በላይ የመሆን፣ የመዘርጋት፣ አዳዲስ ግዛቶችን የመጨመር እና የመብለጥ ዓመታችን ማለት ነው። ይህ ቃል በሕይወታችን አቅጣጫ ሁሉ ተፈጻሚነቱ እውን ነው።

ኢሳይያስ 54
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።
³ በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለሽና፥ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና፥ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋልና።

Category:

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “መስፋፋት | ENLARGEMENT”

Your email address will not be published. Required fields are marked *