በእግዚአብሔር ቤት ለዘላለም እኖራለሁ | I will dwell in the House of the Lord forever
Br90.00
ጌታን ስትቀበሉ እግዚአብሔር ወደ መተከል ያመጣችኋል። ያልተተከለ ነገር አይጠጣም ብሎም አያድግም። ፍሬ የምታፈራው በመዞር ሳይሆን በመተከል እና በመጠጣት ነው። እግዚአብሔር ከማሳደጉ በፊት ሁለት ነገሮች አስፈላጊ ናቸው። ተካዩ እና አጠጪው! ታዲያ ሰው ማወቅ ያለበት የት ጋር ነው የተተከልኩት የሚለውን ነው? አጵሎስ አለ ወይ እዛ ቤት? ተካዩ ጳውሎስ ኖሮ አጠጪ አጵሎስ ከሌለ ችግር አለው፤ እግዚአብሔር ሊያሳድግህ የሚችለው ከበላህ(ከተመገብክ) ነው። እግዚአብሔር እንዲያሳድግህ ከፈለክ የመጀመሪያ የሚያየው መተከልህን ነው። እያንዳንዱ ክርስቲያን መተከልና ተተክሎ ፍሬ ማፍራት አለበት። የተተከለ ማንኛውም ነገር ያድጋል፣ ያፈራል። ፍሬ ከሌለን የመጀመሪያው መጠየቅ ያለብን ነገር ተተክያለሁ ወይ ነው? ምክንያቱም ያልተተከለ ነገር አያድግም፣ ፍሬ አያፈራም።
ለማደግ የት ቤተ ክርስቲያን ልተከል ትላለህ? መንፈሳዊ ሕይወትህን ሊያሳድግልህ የሚችል ጥሩ ምግብ ያለበት ቦታ። ሁሉም ሆቴሎች እኩል እንዳልሆኑ ሁሉም መጋቢዎችም አንድ ዓይነት አይደሉም። የተተከለ እና የጠጣ እግዚአብሔር ያሳድገዋል። ከተተከላችሁ በፍጹም ዲያብሎስ እንዲነቅላችሁ መፍቀድ የለባችሁም። እየጠጣህ ቀጥል ከዛም በኋላ እግዚአብሔር ያሳድግሃል። አሜን!
💒 በእግዚአብሔር ቤት ለዘላለም እኖራለሁ
💿 14 ክፍሎች
🎧 የ21:26:15 ሰዓት Mp3
💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
“ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።”
— መዝሙር 23፥6
☆ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ አንድ ቃል ሕይወትዎ ለዘላለም ይለወጣል።
Reviews
There are no reviews yet.