ትጋት | DILIGENCE

(1 customer review)

Br50.00

“ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፤ ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው።”
— ምሳሌ 12፥27

ብዙዎቻችን ትልቁ ጠላታችን ሰይጣን ነው እንላለን፤ ነገር ግን ልናውቅ የሚገባው ለእራሳችን ትልቁ ጠላት እኛው እራሳችን ነን። ጠላት እኛ እስከፈቀድንለት ድረስ ብቻ ነው በሕይወታችን እድል ሊያገኝ የሚችለው።

ብዙ ሰው የከበረ ሀብት ምንድን ነው ሲባል ወርቅ፣ ገንዘብ ወዘተ ይላሉ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ በአንድ ነገር እንዲመጡ አያውቁም፤ እርሱም በከበረው ሀብት በትጋት ነው። ትጋት ምን እንደሆነ፣ ለምን እንደሚጠቅም፣ የት እንደሚገኝ፣ እንዴት እንደሚገኝ እና መቼ እንደሚገኝ ማወቅ በሚገባ ትጋትን አውቀን በዛ እንድንመላለስ ያስችለናል።

ትጋት ማለት በግሪክ SPODAZO (ስፓዳዞ) ሲሆን ትርጉሙም ፍጥነትን መጠቀም፣ ጥረት ማድረግ ሲሆን የማይበርድ ጥረት፣ በጽናት የሚደረግ ሥራ፣ በሙሉ ኃይልና ጥንቃቄ የሚደረግ ሥራ ማለት ነው። እንዲሁም የአንድ ሰው ጽናትና ጥንቃቄ የተሞላበት፣ ጠንካራ፣ ጽናት እና ቀጣይነት ያለው ስራ እንዲያከናውን ያስችለዋል።

ትጉ ሰዎች ሥራን የመፈጸም አቅም አላቸው!

መጽሐፍ ቅዱስ በትጋት የሚሰሩ ሰዎች እጃቸው መልካም ነገር እንዲያጭዱ ይነግረናል። በተመሳሳይ መልኩ ሰነፍም ሰንፎ ብቻ አይቀርም በስንፍናው ምክንያት የሚቀበለው ደሞዝ አለው እርሱም ድኅነት ነው።

“የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፤ የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች።”
— ምሳሌ 10፥4

ትጋት መቸኮል እንጂ መዘግየት፣ ራስን መቻል እንጂ ሸክም መሆን፣ ጥረትን ማድረግ እንጂ ለዘብተኛ መሆን አይደለም። በመሆኑም በክርስትና ሕይወታችን እንዲሁም በሁሉም የሕይወታችን አቅጣጫ ልንይዘው እና ልንገለጥበት የሚገባ መንፈሳዊ ባህሪይና ሀብታችን ነው።

Category:

1 review for ትጋት | DILIGENCE

  1. Daniel

    Thanks

Add a review

Your email address will not be published. Required fields are marked *