Description
“ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።”
— ማቴዎስ 16፥16
✍️ ኢየሱስ ክርስቶስ መሲህና የእግዚአብሔር ልጅ ነው!
የእግዚአብሔር ልጅ ነው ስንል እያልን ያለነው እግዚአብሔር ነው ማለታችን ሲሆን፤ የትየሌለነቱን የሚያስረዳ ነው። ቤተክርስቲያን የተመሰረተችበትም ዋነኛ መሠረት “አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” በሚለው መገለጥ ነው።
እንግዲህ አይሁድ፣ ኢየሱስ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን አባቱ በማድረግ፣ ራሱን ከእግዚአብሔር እኩል በማድረጉ፣ ሊገድሉት አጥብቀው ይፈልጉት ነበር።
— ዮሐንስ 5:18
እኛ ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ ያለን መረዳት ክርስትናን በሚገባ እንድንኖር ወይንም እንዳንኖር ያደርገናል። ምክንያቱም ክርስቲያንን ክርስቲያን የሚያደርገው ስለ ክርስቶስ ባለው ጥልቅ እውቀት ላይ የተመሰረተ ነው።
THERE IS NO CHRISTIANITY AND CHRISTIANS WITHOUT CHRIST!
ታዲያ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ልጅነቱ ወይም ባሻገር ደግሞ በዚህ መልኩ በጥቂቱ ተገልጧል…
እኔ ሕያው ነኝ፤ ሞቼ ነበር፤ እነሆ፤ አሁን ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦል መክፈቻም በእጄ ነው።
— ራእይ 1:18
“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።”
— 1ኛ ዮሐንስ 5፥20
“እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16
“ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ”
— 1ኛ ዮሐንስ 3፥9
የምናመልከው ኢየሱስ የሐይማኖት መምህር ሳይሆን ብርሃን የሆነ የሕይወታችን ትርጉም፣ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። በስጋ ውስጥ አድሮ የመጣ የዲያብሎስን ስራ በማፍረስ የተገለጠ ነው። የመጣውም ለእኛ ያለው ፍቅር አስገድዶት እኛ የጠፋነውን ለማዳን ነው።
ታዲያ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን!
“የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው።”
— ሉቃስ 19፥10
Reviews
There are no reviews yet.