እምነት | FAITH — Volume 01

Br90.00

Category:

Description

“እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።”
— ዕብራውያን 11፥1

በእግር ኳስ ህግ ውስጥ በእጅ መንካት የተከለከለ እንደሆነው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ጉዞ ያለ እምነት አብረነው ልንጓዝ አንችልም። እግዚአብሔር የሚባለው አምላክ ከእምነት ውጪ አይሰራም፤ በእምነት ከተጓዝን ግን እናስደስተዋለን ከእምነት ውጪ ከተጓዝን ደግሞ አናስደስተውም።

እምነት በቤተክርስቲያን ታሪክ ያስፈላጊነቱ ያህል ከፍተኛ አለመረዳት፣ ስደትና ተቃውሞ ከደረሰባቸው ትምህርቶች አንዱ ነው። ነገር ግን ክርስቲያን በሕይወቱ ሊረዳውና ሊገነዘበው ከሚገባው የእግዚአብሔር ቃል እውነቶች መካከል እምነት አንዱ እና ወሳኙ ነው።

እምነት ዘመን ያመጣው ትምህርት ሳይሆን ከሰው ፍጥረት እስከ ሰው ፍጻሜ ድረስ የሚቀጥል እውነት ነው። የሰው ልጅ በኃጢአት የወደቀው እግዚአብሔር የነገረውን ነገር መጀመሪያ ባለማመኑ ቀጥሎም ባለመታዘዙ ሲሆን እንዲሁም በመጨረሻም ሰው ወደ ሲዖል የሚሄደው ጌታ ኢየሱስን ባለማመኑ ምክንያት ነው።

ለእምነት አባቶቻችን የተመሰከረው የሕይወት ዘይቤያቸው እምነት ስለሆነ ነው። እኛም ጌታ ኢየሱስን አምነን ሕይወታችንን እንደጀመርን በእምነት በመኖር እንቀጥል፤ እግዚአብሔርን እናስደስት።

ዕብራውያን 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና።
³ ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “እምነት | FAITH — Volume 01”

Your email address will not be published. Required fields are marked *