እግዚአብሔር እረኛዬ ነው | God is My Shepherd
Br50.00
ስንሄድ ስንሄድ በህይወት ጎዳና የምንሄድበት መንገድ ጠፍቶን በተቅበዘበዝንበት ጊዜ ወደ ነፍሳችን እረኛና መሪ ተመልሰን ለመኖር ምንም የማያስፈልገው እግዚአብሔር መጋቢ ሆኖ እየተንከባከበ፣ አስተማሪ፣ ወዳጅ፣ ጓደኛ፣ ገዢ ሆኖ የምንቀሳቀሰውና የሚጎድለን ነገር ሳይኖር በተዋበና በሚያምር፣ በአስደሳች ስፍራ አሰማርቶን ቸርነቱና ምህረቱ ከኃላ፣ እረኛው እግዚአብሔር ሆኖ ነፍሳችንን እየመለሰ አለ። ሰው በእግዚአብሔር እረኝነት ውስጥ ሆኖ በመትረፍረፍ ይኖራል እንጂ የሚያጣው መልካም ነገር የለም። እግዚአብሔርን በእረኝነቱ ማወቅ በህይወታችን ማን ከፌት፣ ማን ከኃላ፣ ማን መሪ፣ ማን ተከታይ እንደሆኑ እንድረዳ ያደርገናል።
“እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።”
— መዝሙር 23፥1
BEZUAYEHU TAYE GEBEREKIDAN –
Best Teaching