ክርስቶስ ፈዋሹ | Christ the Healer

(2 customer reviews)

Br90.00

እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ ከፈጠረበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ፈዋሽና መሃሪ አምላክ ሲሆን አዳምንም ሲፈጥረው ፍፁም ሰው ሆኖ ያለ ኃጥያት፣ በሰውነቱ ላይ ደግሞ ሙሉ እና ጤነኛ አድርጎ ነበር። ነገር ግን ኃጥያት ወደ አለም ከገባ በኋላ በሽታ፣ ድህነት፣ ሞትን ወለደ። በዘመናትም መካከል ሁሉ እግዚአብሔር ድንቅ የሆነ ፈዋሽ በመሆኑ ሰውን በመፈወስ ስራው ቀጥሎ ነበር፤ በመጨረሻም ልጁን በመላክ ጤንነታችንን ያካተተውን ለድነት የሚከፈለውን ዋጋ ከፈለልን። የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ለመለኮታዊ ፈውስና ህይወት ዘር ሲሆን እግዚአብሔርም ለፈውስ ያለውን ፈቃድ የምናውቅበት መንገድ ነው። ሰው ፈውስን ከመቀበሉ በፊት መረዳት ያለበት መሠረታዊ ነገር ፈውስ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ነው፤ ይህም ፈውሱን ለመቀበል አንድ እርምጃ ነው። በዚህ ትምህርት ውስጥም ስለ መለኮታዊ ፈውስ፣ መለኮታዊ ፈውስ የሚሰራባቸውን መንገዶች፣ ፈውስ ለማን ነው? እግዚአብሔር ፈወስን ለሁሉ አዘጋጅቷልን? ፈውስ ሁልጊዜ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውን? እግዚአብሔር ቀድሞ ይፈውስ እንደነበረው አሁንም ይፈውሳልን? ለሚሉት ጥያቄ መልስ በማግኘት “እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚያምነው በጤንነት እና ፍላጎቱም በጤንነት እድንኖር ነው” የሚል እምነትን እናዳብራለን።

“እርሱም፦ አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም የሚበጀውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ።”

— ዘጸአት 15፥26

“በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ፦ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።”
— ማቴዎስ 8፥16-17

“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”

— ኢሳይያስ 53፥5

💿 ክርስቶስ ፈዋሹ || Christ the Healer
◇ 30 ክፍሎች
🎧 የ34:41:31 ሰዓት Mp3
💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

☆ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ አንድ ቃል ሕይወትዎ ለዘላለም ይለወጣል።

2 reviews for ክርስቶስ ፈዋሹ | Christ the Healer

  1. ግርማ

    እጅግ በጣም ወሳኝ እና ድንቅ ትምህርት

  2. Asefash Kassa

    I want listen and healed

Add a review

Your email address will not be published. Required fields are marked *