የሰው ልብ | A Man’s Heart
Br90.00
እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ሲመለከት ቁመናችን፣ መልካችን፣ አካሄዳችን እንዲሁም ሌላ በውጭ የሚታየው አኳኋናችንን በማየት እንደማይማረክ ልናውቅ ይገባል። ምክንያቱም እግዚአብሔር ፊትን ሳይሆን ልብን የሚያይ እና የሚመረምር አምላክ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ሰው ሁለንተና አለው፤ ከሁለንተናው ባለፈ ግን በጣም በትኩረት ሊሰራበት የሚገባው ልብ አለው። ይህም ልብ የተደበቀ ሀሳብ እና ፈቃድ የያዘ የእግዚአብሔር ቃል ብቻ የሚያውቀው እና የሚመረምረው ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልባችን የተጠቀሰው ከእምነት፣ ባህርይ፣ ህሊና፣ ስነ ምግባራዊ ባህርይ፣ ድፍረት፣ ፈቃድ፣ ማስተዋል፣ ስሜት፣ ፍላጎት እና የመሳሰሉት ጋር ነው። ታዲያ ልባችን ምንድነው የሚለውን መረዳት እና ከመንፈሳችንና ከነፍሳችን የተለየ መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ሲሆን፤ ሊመረምረው የሚችለው ቃሉ ጋር በመቅረብ ልናስፈትሽ እና ልንቃኘው ይገባል።
💿 የሰው ልብ | A Man’s Heart
◇ 21 ክፍሎች
🎧 የ27:36:57 ሰዓት Mp3
💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
Reviews
There are no reviews yet.