የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ | The Resurrection of Jesus Christ

Br50.00

Description

ሮሜ 6:8-10
[8] ከክርስቶስ ጋራ ከሞትን፣ ከርሱ ጋራ እንደምንኖር እናምናለን። [9] ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷልና፣ ዳግመኛ እንደማይሞት እናውቃለን፤ ሞት ከእንግዲህ በርሱ ላይ ጕልበት አይኖረውም። [10] በሞተ ጊዜ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኀጢአት ሞቷል፤ ነገር ግን በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖራል።

✍️ በአንድ ወቅት በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በህመሙ ጽኑ መሆን የተነሳ ለመኖር 15 ቀን ብቻ እንዳለው የተነገረው ሰው ነበር። ታዲያ ሐኪሙ የነገረውን እንደ መርዶ ከመውሰድ ይልቅ ታላቅ የምስራች እንደተነገው አድርጎ በጣም ይደሰታል። ሐኪሙም ሊሞት እንደሆነና መርዶ እንደሆነ ድጋሜ በማስረዳት፤ ለምን በተቃራኒው እንደተደሰተ ይጠይቀዋል። እርሱም የተደሰትኩት ከ15 ቀን በኋላ በጣም የምወደውን እና የምናፍቀውን ጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስ ላየው፣ ላገኘው እና ለዘላለም ከእርሱ ጋር ልኖር ስለሆነ ነው ብሎ ይመልሳል።

በትንሳኤ የሚያምኑ ክርስቲያኖች ሞት ለእነርሱ መሸጋገሪያ እንጂ ማብቂያ እንዳልሆነ የሚረዱ ናቸው። በትንሳኤው የተፈጸሙ ነገሮች ጥልቅ ስነ-መለኮታዊ እውነታዎች መሀከል ኢየሱስ የእኛን የኃጢአት እዳ ሁሉ ከፍሎ በተጨማሪም አጽድቆናል፣ የሞት ኃይል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሸንፏል፣ ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን መነሳቱ በተጨማሪም ትንሳኤው የአዲስ ፍጥረት መሠረት መሆኑ ናቸው።

የትንሳኤው ኃይል በእኛ ሕይወት ውስጥ መንፈሳዊ ተሐድሶን፣ በኃጢአት ላይ ድል እና ለእግዚአብሔር ለመኖር ኃይልን ሰጥቶናል። ትንሳኤው የሰጠን ተስፋ ደግሞ የሙታን ትንሳኤ እና ሞትን ለመጨረሻ ጊዜ ማሸነፍ ነው።

We worship a living Savior, not a dead prophet!

ለትንሳኤው ልንሰጠው የሚገባው ምላሽ በትንሳኤው ማመን፣ የትንሳኤውን ጌታ ማምለክ፣ የትንሳኤውን ሕይወት መኖር እና ትንሳኤውን በድፍረት መስበክ ነው።
The Early Church’s boldness and power came from the resurrection message.

“ሐዋርያትም ስለ ጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ በታላቅ ኀይል መመስከራቸውን ቀጠሉ፤ በሁላቸውም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበር።”
ሐዋርያት ሥራ 4:33 (አ.መ.ት.)

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ | The Resurrection of Jesus Christ”

Your email address will not be published. Required fields are marked *