የእግዚአብሔርን ቃል በሕይወታችን መለማመድ | Exercising the Word of God in our lives
Br50.00
“ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥8
የሰው ሕይወት እንደምናውቀው የሚያስበው ሀሳብ ድርጊት፣ ድርጊቱ ደግሞ ልምምዱ እንደሚሆን ግልጽ ነው። በዚህም ምክንያት ሰው አሁን የሆነውን የሆነው እንዲሆን የሚያስችለውን ነገር በተደጋጋሚ በማድረጉ ነው። አንድ ነገር ለመለማመድ የእኛ እስኪሆን ድረስ በተደጋጋሚ ማድረግ ይጠበቅብናል። እንዲሁም የተለማመድነው ነገር በሕይወታችን እንዲገለጥ እና ውጤት እንዲያመጣ ደጋግመን ልንተገብረው ይገባል።
ልናውቅ የሚገባው ነገር በሕይወታችን ላይ ደጋግመን የምናደርገው ነገር ለውጥን ያመጣል። ስለዚህ የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል የተተገበረ፣ የተፈጸመ፣ መንፈሳችን ጋር የደረሰ እና በሕይወታችን ላይ የተገለጠ እንዲሆን ደግሞ ልናስበው እና ልናሰላስለው ይገባል። ማሰላሰል አንዱ በሕይወታችን ቃሉ ውጤት እንዲያመጣ የሚያደርግ ትልቁ መንገድ ሲሆን የእግዚአብሔርን ቃል ከፊደል ባለፈ ገጽታው እንድንለማመደው ይረዳናል።
በእግዚአብሔር ቃል አግባብ መሠረት ማሰላሰል የጀመረ ሰው በዛ ሀሳብ ያለውን የቃሉን ኃይል የመቀበል መብት አለው።
Reviews
There are no reviews yet.